በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮርያ የውሃ ውስጥ የኑክሌር ድሮን ሞከረች


የሚሳኤል ሙከራውን በቲቪ ሲታይ
የሚሳኤል ሙከራውን በቲቪ ሲታይ

ሰሜን ኮርያ አዲስ በውሃ ውስጥ የሚሠራ የኑክሌር ጥቃት መፈጸሚያ ድሮን መሞከሯን የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።

በጠላት የውሃ ድንበሮች ውስጥ የራዲዮ አክቲቭ ጨረር ሱናሚ የሚፈጥር ነው ተብሎለታል።

ድሮኑ ከሩሲያው ፖሲዶን ሱፐር ቶርፒዶ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነም ተነግሯል።

ሙከራው በአገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን መሪነት ለሶስት ቀናት የሚደረግ ወታደራዊ ልምምድ አካል ነው ተብሏል።

የድሮኑ ዓላማ በውሃ ውስጥ የሚመጡ የጠላት መሳሪያዎችን ማፈዳትና የጨረር ሱናሚ መፍጠር ነውም ተብሏል።

ባለፈው ማክሰኞ በተጀመረው ሙከራ ድሮኑ ለ59 ሰዓታት ውሃ ውስጥ መቆየቱንና፣ ለሙከራ የተቀመጠለትን ኢላማም ማፍረራረሱ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG