በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኪም ጆንግ ኡንና ቭላዲሚር ፑቲን - በቭላዲቫስቶክ


የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር በያዝነው ሳምንት ቭላዲቫስቶክ ወደ ተባለችው የሩቅ ምስራቅ የሩስያ ከተማ ይጓዛሉ።

የሩስያ ቤተ መንግሥት/ክረምሊን/ በበኩሉ ሁለቱ መሪዎች በመጪው ሀሙስ እንደሚሰበሰቡ አረጋግጧል። ሰሜን ኮርያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የምታደርገው የኑክሌር ንግግር ባለበት በቆመበት በአሁኑ ወቅት ማዕቀቦች እንዲነሱላቸው በፑቲን ላይ ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኪም ጆንግ ኡን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እንዲሁም ከቪየትናም፣ ቻይናና ደቡብ ኮርያ መሪዎች ጋር በከፍተኛ ደርጃ የታዩ ስብሰባዎች አካሂደዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG