በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኪም ጆንግ ኡን እና ቭላዲሚር ፑቲን ሞስኮ ለመገናኘት አቀዱ


የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን በያዝነው የአውሮፓ ወር መጨረሻ ሞስኮ ላይ ለመገናኘት አቅደዋል።

የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ ዕቅድ ከክሬምሊን የወጣው ፒዮንግያንግ እጅግ ኃይለኛ የተባለ አረር አዘል ሥልታዊ የጦር መሣሪያ መሞከሯን ካሳወቀች በኋላ ነው።

ስለሁለቱ መሪዎች መነጋገሪያ ጉዳዮች ከሞስኮ የወጣ ዝርዝር ማብራሪያ ባይኖርም ስብሰባው ግን ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብሰበት የቆየ መሆኑን ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል።

ሰሜን ኮሪያን ኒኩሌር ትጥቋን ለማስፈታት በሚል በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በኪም ጆንግ ኡን መካከል ሁለት ዙር ስብሰባ የተካሄደ ቢሆንም ጉዳዩ እስከ አሁን ያለመፍትኄ እንደተንጠለጠለ ነው።

ሁለቱም መሪዎች ለሦስተኛ ጊዜ የመገናኘት ሃሣብ አንፀባርቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG