ዋሺንግተን ዲሲ —
በደቡብ ኮሪያው የአንድነት ሚኒስትር ቻኦ ማይኡንግ ግዮንገለጣ መሠረት፣ የቃል ኪዳን ሰፈር ተብሎ በሚታወቀውና ደቡቡንና ሰሜኑን የሚለየው ቀጣና በሚገኝበት ጳንሙንጆም ከሰሜን ኮሪያ ዲፕሎማቶች ጋር ይወያያሉ።
ውይይቱ፣ እአአ ካለፈው ታህሣሥ 2015 ወዲህ፣ በሲኦል እና በፒዮግያንግ መካከል በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄድ የመጀመሪያው ግንኙነት እንደሚሆንም ታውቋል።
የሰሜኑ መሪ ኪም ጆንግ ኡንም፣ በአዲስ ዓመት መግቢያ ንግግራቸው፣ ፕዮንግያንግ፣ ለክረምቱ ኦሊምፒክ ውድድር፣ ስፖርተኞቿን ወደ ደቡብ ኮሪያ ለመላክ እያሰበችበት መሆኗን መጥቀሳቸው ይታወሳል።
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ለመወያየት ያሳየችው ፈቃደኝነት “ተስፋ ከመቁረጥ የመነጨ ነው” ሲሉ ባለፈው ማክሰኞ ትዊት አድርገዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ