በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የግጭት አካባቢዎች የጤና ሥርዓቱ ክፉኛ መዳከሙ ተገለጸ


በኢትዮጵያ የግጭት አካባቢዎች የጤና ሥርዓቱ ክፉኛ መዳከሙ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:23 0:00

በኢትዮጵያ የግጭት አካባቢዎች የጤና ሥርዓቱ ክፉኛ መዳከሙ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ግጭት በተካሔደባቸው አካባቢዎች የጤና ሥርዓቱ ክፉኛ መዳከሙን የገለጸው “ፕሮጀክት ሆፕ” የተባለ የጤናው ዘርፍ ግብረ ሠናይ ድርጅት፣ በትግራይ ክልል የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት ሦስት በመቶ ብቻ እንደሆኑ አመላክቷል፡፡

ግጭት በቀጠለባቸው በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎችም “የጤና ሥርዓቱ ይበልጥ አሳሳቢ ሆኗል፤” ያሉት የ“ፕሮጄክት ሆፕ” የአፍሪካ ቀጣናዊ ዲሬክተር ስቲቨን ኔሪ፣ የእንቅስቃሴ ገደቦች ችግሩን እንደሚያባብሱት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ለተፈናቀሉ 60ሺሕ ለሚደርሱ ዜጎች፣ የተለያዩ የጤና እና አስቸኳይ የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ መደረጉንና ይህም በኦሮሚያ ምዕራባዊ ዞኖች መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮም በ“ፕሮጀክት ሆፕ” መግለጫ ላይ አስተያየት ሰጥቶናል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG