በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አካሄደች


ፎቶ ፋይል፦ የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ የባለስቲክ ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራዎችን ሲመለከቱ
ፎቶ ፋይል፦ የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ የባለስቲክ ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራዎችን ሲመለከቱ

የሰሜን ኮሪያ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት የአጭር ርቀት የባለስቲክ ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራዎችን በዛሬው እለት አካሂዳለች፡፡

ይህኛው በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የዲፕሎማሲያዊ ጫና ለማሳደር የታሰበ የቅርብ ጊዜው ጥረቷ መሆኑን ተነግሮለታል፡፡

እንዲህ ያሉ ሙከራዎችን የሚከታተለው የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ክፍል፣ የደቡብ ኮሪያ ሚሲኤሎች፣ 800 ኪሎ ሜትር ያህል መጓዝ እንደሚችሉና፣ 60 ኬሎሜትር ወደ ላይ ከተወነጨፉ በኋላ ቁልቁል በመውረድ በሰሜን ኮሪያ ምስራቃዊ ክፍል ወደሚገኘው ውሃ እንደሚጠልቁ አስታውቀዋል፡፡

የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር ሚሳኤሉ ወደ ጃፓን የግዛት ክልል አለመግባቱና ከአገሪቱ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ክልል ውጭ ያረፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዩናይትድ ስቴትስ ኤንዶ ፓስፊክ ወታደራዊ የማዘዣ ማዕከል የወጣው መግለጫ ደግሞ ሙከራው “አለመረጋጋት ፈጣሪ የሆነውን የሰሜን ኮሪያን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ፕሮግራም ይዘት በግልጽ ያሳያል” ብሏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ እኤአ ከ2019 ጀምሮ በርካታ አጫጭር የባለስቲክ ሚሳኤል መሳሪያዎችን የሞከረች ቢሆንም ያሁኑ ምን ዓይነት ሚሳኤል እንደሆነ አለመታወቁ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG