በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በሰሜን ኮሪያ የሰብአዊ መብቶች መልዕከተኛ እንዲመድቡ ተጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ ሰሜን ኮሪያ ውስጥ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመቃወም የተካሄደው ሰልፍ፣ ሲኦል፤ ደቡብ ኮሪያ
ፎቶ ፋይል፦ ሰሜን ኮሪያ ውስጥ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመቃወም የተካሄደው ሰልፍ፣ ሲኦል፤ ደቡብ ኮሪያ

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እኤአ ከጥር 2017 ጀምሮ ክፍት በሆነው በሰሜን ኮሪያ የሰብአዊ መብቶች ልዩ መልዕክተኛ ቦታ አዲስ ሰው እንዲመድቡ ጠየቁ፡፡

እኤአ በ2004 የወጣው የሰሜን ኮሪያ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ለዚህ ስፍራ የተመበደ ሰው በፕሬዚዳንቱ እንዲመረጥና በዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አማይካነት ጸድቆ እንዲሾም የሚያዝ መሆኑን በጥያቄው ተመልክቷል፡፡

ይህ ቦታ ባዶ የሆነው እኤአ በ2018 ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆን ኡን ጋር፣ ሲንጋፑር ላይ ተገናኝተው ከተነገጋሩ በኋላ፣ የቦታው አስፈላጊነት ችላ በማለታቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

የቪኦኤ የኮሪያ ስርጭት አገልግሎት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተደጋጋሚ ጊዜ ጥያቄውን ማቅርቡ የተገለጸ ሲሆን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በኤሜል በሰጡት ምላሽ

“ይህን አስመልክቶ በአሁን ሰዓት አስተዳደሩ ይህን ብሏል ብዬ የምስጣችሁ ምንም ነገር የለም” ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አያይዘው

“ይሁን እንጂ በሰሜን ኮሪያ ያለው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የውጭ ፖሊሲያችን ዋነኛው ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ይቀጥላል” ማለታቸው ተመልክቷል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች የእስያ መምሪያ ረዳት ድሬክተር ፊል ሮበርትሰን “በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ በትልቁ እጨነቃለሁ የሚል አስተዳደር በሰሜን ኮሪያ ያሉትን የሰብ አዊ መብቶች ጥሰት አስመልክቶ አፋጣኝ እምርሃ መውሰድ አለበት” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG