በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ በጃፓን ሰማይ በኩል ባሊስቲክ ሚሳዬል ተኮሰች


ሰሜን ኮሪያ የባሊስቲክ ሚሳዬል ማስፈንጠሯን በተመለከተ ዘገባ እየተሰራጨ።
ሰሜን ኮሪያ የባሊስቲክ ሚሳዬል ማስፈንጠሯን በተመለከተ ዘገባ እየተሰራጨ።

ሰሜን ኮሪያ ለግዜው ዓይነቱ በውል ያልታወቀ መካከለኛ ርቀት ባሊስቲክ ሚሳዬል በጃፓን አናት ላይ አስፈንጥራለች። ቶኪዮ በሁለት የሰሜን ግዛት ያሉ አንዳንድ ዜጎቿን ለጥንቃቄ ለማሰወጣት ተገዳለች።

ለዓመታት ያልታየ ጸብ አጫሪነት ነው ተብሏል።

የጃፓን መከላከያ ሚኒስትር ያሱካዙ ሃማዳ እንዳሉት ሚሳዬሉ ለአንድ ደቂቃ ወይም ለ4ሺህ 600ኪሜ ያህል በጃፓን አናት ላይ ከበረረ በኋላ፣ ከጃፓን በስተምስራቅ 3ሺ 200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሰላማዊ ውቅያኖስ ውስጥ አርፏል።

የጃፓኑ የካቢኔ ጸኃፊ ሂሮካዙ ማትሱሮ በበኩላቸው ሚሳዬሉ በሃገሪቱ አቆጣጠር ዛሬ ጠዋት 7 ሰዓት ከ 22 ደቂቃ ላይ ተተኩሶ፣ በሰላማዊ ውቅያኖስ “የጃፓን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን” ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል ላይ ከ22 ደቂቃ በኋላ አርፏል።

ዛሬ የመንበረ ሥልጣናቸውን አንደኛ ዓመት ያከበሩት የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ የሚሳዬል ውንጨፋውን አውግዘዋል።

ሰሜን ኮሪያ ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ አምስት ግዜ የሚሳዬል ሙከራ ያደረገች ሲሆን፤ ከዚህ በፊት በ2017 ሁለት ሙከራዎች በጃፓን ግዛት በኩል ስታደርግ ዜጎች እንዲጠለሉ ማስጠንቀቂያ ለማውጣት ተገዳለች።

በኮሪያ ባህረ ገብ መሬት ሰሞኑን ውጥረቱ እያየለ መጥቷል። ሰሜን ኮሪያ አምስቱን ሙከራዎች ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ ያደረገቸው፣ በአሜሪካና በደቡብ ኮሪያ መካከል ከፍተኛ የባህር ላይ የጋራ ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ ዮል ቅዳሜ ዕለት በተከበረው የጦር ኃይሎች ቀን ላይ ባሰሙት ንግግር፣ የኑዩክሌር ትንኮሳውን በተመለከተ ሰሜን ኮሪያን አስጠንቅቀው፣ የኑዩክሌር ኃይልን ለመጠቀም ከወሰነች “ቆራጥ እና ከባድ” መልስ ከአጋሮቿ ይሰጣታል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG