በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የእስያ ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ ሰሜን ኮሪያ የሚሳዬል ፍተሻዎችን አካሄደች


ደቡብ ኮሪያ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ ሰዎች የሰሜን ኮሪያ የሚሳዬል ሙከራ የዜና ዘገባ ሲመለከቱ፤ ሲዖል፣ ደቡብ ኮሪያ፤ እአአ ግንቦት 25/2022
ደቡብ ኮሪያ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ ሰዎች የሰሜን ኮሪያ የሚሳዬል ሙከራ የዜና ዘገባ ሲመለከቱ፤ ሲዖል፣ ደቡብ ኮሪያ፤ እአአ ግንቦት 25/2022

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሰሜን እስያ ጉብኘታቸውን ባጠናቀቁ ጥቂት ሰዓታት ውስጥ፣ ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ረቡዕ አህጉር አቋራጭ እንደሆነ የተገመተውን ጨምሮ ሦስት የባለስቲክ ሚሳዬል መሳሪያዎችን ለፍተሻ መተኮሷን ደቡብ ኮሪያ አስታወቀች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ባይደን እስያን በሚጎበኙበት ወቅት የረጅም ርቀትሚሳዬሎችን፣ ሌላው ቀርቶ የኒውከለር ሙከራን ልታካሂድ እንደምትችል አስቀድመው አስጠንቅቀዋል፡፡

ምንም እንኳ ሰሜን ኮሪያ ባይደን እስያን እየጎበኙ በነበረበት ወቅት ከሙከራው የታቀበች ቢሆንም ጃፓንን ከለቀቁ 12 ሰዓታት በኋላ ሙከራዎችን አከታትላ ለቃለች፡፡ የመጀመሪያው ሚሳዬል አሲቢኤም ተብሎ የሚጠራው ሲሆን በ540 ኪሜ ከፍታ 340 ኪሜ መጓዝ የሚችል መሆኑን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል፡፡

በአጸፋው ደቡብ ኮሪያ 30 ኤፍ 15 ኬ የተባሉ ተዋጊ ጄቶችን ያካተቱ የጦር ልምድድ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡ ደቡብ ኮሪያና ዩናይትድ ስቴትስ የምድር ለምድር ሚሳኤል ሙከራዎች ማድረጋቸውን የደቡብ ኮሪያ ጦር መግለጫ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት 17 ጊዜ የጦር መሳሪያ ፍተሻዎችን ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን አህጉር አቋራጭ ሙከራዎችን ሲታደርግ በዓመቱ ውስጥ ይህ የመጀመሪያው መሆኑ ተመልክቷል፡

ዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ኮሪያና ጃፓና የሰሜን ኮሪያን ሙከራዎች የተባበሩ መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትን ውሳኔዎች በመጣስ የተፈጸመ መሆኑን በመጥቀስ ተቃውመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ቻይናና ሩሲያ ዩናይትድ ስቴትስ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ከሥምምነት አለመድረሷን በመጥቀስ ወቅሰዋል፡፡

XS
SM
MD
LG