በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያው መሪ የሚሳዬል ሙከራውን በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል


የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ሲመለከቱ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ሲመለከቱ

የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን አገራቸው ትናንት ያደረገቸውን የሃይፐርሶኒክ ሚሳዬል ሙከራ በቦታው ተገኘተው መመልከታቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ገልጹ፡፡

የሰሜን ኮሪያ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ፕሬዚዳንት ኪም የቆዳ ጃኬታቸውን ለብሰው አጎልቶ በሚያሳያ መንጽር ከሚሳዬል መወንጨፊያው ጣቢያ ከሚመስል ስፍራ ሆነው ሲመለከቱ የሚያሳየውን ምስል አሰራጭተዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ ባላፈው ማክሰኞ የተኮሰችው የሙከራ ሚሳዬል እንደተፈለገው መዘወር የሚቻልና 1ሺ ኬሎሜትር ርቀት ላይ ያለ ኢላማውን አሳምሮ ሊመታ የሚችል መሆኑን፣ የሰሜን ኮሪያ ዜና አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ይህ ባላፈው ማክሰኞ ከተገመተው የበለጠ ርቀት የሚጓዝ ቢሆንም፣ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ባለሥልጣናት ግን መጓዝ የሚችለው የ700 ኪሜትር ርቀት መሆኑን ገልጸው ያም ቢሆን እጅግ የተሻሻለው መሳሪያ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አሁን የተሞከረው ሚሳዬል ከድምጽ ፍጥነት 10 ጊዜ እጥፍ ፈጥኖ ሊጓዝ የሚችል መሆኑን ባለሥልጣትን ጠቅሶ የሰሜን ኮሪያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ ባለሙያዎች ግን አብዛኞቹ ሚሳዬሎች ዛሬ ከድምጽ ፍጥነት አምስት ጊዜ በላይ ፈጥነው የሚጓዙ /ሃይፐርሶኒክ/ መሆናቸውን ገልጸው፣ ዋናው ነገር ሚሳዬሎቹን ምን ያህል እንደ ልብ መዘወርና ኢላማዋችን በትክክል መምታት እንደሚችሉ ማወቁ ወሳኝ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ከረጅም ጊዜ በኋላ የፕሬዚዳንቱ በቦታው ተገኝቶ መመልከትና ስለ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዬሎቹ አጋኖ መናገሩ ለፖለቲካ ፍጆታ የዋለ ፕሮፖጋንዳ ሊሆን እንደሚችልም ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG