በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቀጣዩ የዓለም የጤና ድርጅት መሪ ማን ይሆን?


የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አዳህኖም
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አዳህኖም

“በሀገር አቀፍ ፈረጃ የኢትዮጵያን የጤና አቅርቦት ሥርዓት ለማሻሻል የተወጠነ የተሃድሶ ዕቅድ በመምራትና በመርዳት አገልግያለሁ። ... ውጤትም አግኝቻለሁ። በዓለም አቀፍ ደረጃም ዋና ዋና የሚባሉትን ዓለም አቀፍ የጤና አገልግሎት ተቋማት በቦርድ ሰብሳቢነት አገልግያለሁ።” - የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ

“በሀገር አቀፍ ፈረጃ የኢትዮጵያን የጤና አቅርቦት ሥርዓት ለማሻሻል የተወጠነ የተሃድሶ ዕቅድ በመምራትና በመርዳት አገልግያለሁ። ... ውጤትም አግኝቻለሁ። በዓለም አቀፍ ደረጃም ዋና ዋና የሚባሉትን ዓለም አቀፍ የጤና አገልግሎት ተቋማት በቦርድ ሰብሳቢነት አገልግያለሁ።” -የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አዳህኖም

“ትልቁ አቅሜና ያለሙንም የጤና ድርጅት በቅጡ ሊረዳ የሚችለው? .. መልሱ የሌለኝ ጉዳይ እንደሚሆን አውቃለሁ። የማላውቀው ነገር ሲገጥመኝ፤ ትክክለኛውን መልስ እስካገኝና ሥራው ዳር እስኪደርስ እቀጥላለሁ።” ይላሉ። ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር፤ ፓኪስታናዊቱ የልብ ሃኪምና ደራሲ

ፓኪስታናዊቱ የልብ ሃኪምና ደራሲ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር
ፓኪስታናዊቱ የልብ ሃኪምና ደራሲ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር

“የሥራ ልምዴን የሚያሳየውን ማሕደር ተመልከቱ፣ ፈትሹ። አመርቂ ውጤት ማምጣት የሚቻል መሆኑን በሚያሳየው መዋቅር ለውጥ ማምጣት መቻሌን ታጤናላችሁ።” እንግሊዛዊው ዶ/ር ዴቪድ ናባሮ

እንግሊዛዊው ዶ/ር ዴቪድ ናባሮ
እንግሊዛዊው ዶ/ር ዴቪድ ናባሮ

የዓለሙን የጤና ድርጅት/WHO/ን ለመምራት ለአንድ ዓመት የዘለቀው ውድድር ከመጨረሻው ዙር ላይ ደርሷል።

የቀጣዩ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ምርጫ ውሳኔ የፊታችን ግንቦት ይፋ ይደረጋል።

ሦስቱ ተፎካካሪዎች በማራቶን ፍጥነት በተከታታይ ባካሄዷቸው ጋዜጣዊ ጉባዔዎች የዓለሙን ጤና ድርጅት ለመምራት ብቁ ያደርጉናል ያሏቸውን የሞያ ልምዶችና ብቃት፤ እንዲሁም ድርጅቱን ይበልጥ ስኬታማ ለማድረግ እና ለተሻለ ደረጃም ለማብቃት ያስችሉናል የሚሏቸውን የዕቅድ ሃሳቦች አቅርበዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዓለም የጤና ድርጅት /WHO/ን ለመምራት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ዕጩ ናቸው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቀጣዩ የዓለም የጤና ድርጅት መሪ ማን ይሆን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:21 0:00

XS
SM
MD
LG