በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ 19 ክትባት እንዲሠራ ያስቻሉ ኖቤል ተሸለሙ


ካታሊን ካሪኮ በሃንጋሪ ሰገድ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር፣ ድሩ ዋይስማን በዩናይትድ ስቴትሱ ፔንሲቬንያ ዩኒቨርስቲ ፔሪልማን የሕክምና ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሰር
ካታሊን ካሪኮ በሃንጋሪ ሰገድ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር፣ ድሩ ዋይስማን በዩናይትድ ስቴትሱ ፔንሲቬንያ ዩኒቨርስቲ ፔሪልማን የሕክምና ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሰር

ምርምሮቻቸው በኮቪድ 19 ዓለምአቀፍ ወረርሽኝ ወቅት ክትባት እንዲሠራ አስተዋፅዖ ያደረጉ ሁለት ሳይንቲስቶች በሕክምና ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸነፉ።

ካታሊን ካሪኮ እና ድሩ ዋይስማን ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ክትባት እንዲፈጠር ያስቻለ የላቀ ግኝት እንዲጨበጥ ማድረቸውን የሽልማቱ ኮሚቴ አስታውቋል።

ካሪኮ በሃንጋሪ ሰገድ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር፣ እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትሱ ፔንሲቬንያ ዩኒቨርስቲ ፔሪልማን የሕክምና ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሰር ሲሆኑ ዋይስማን ደግሞ በፔን ኢንስቲትዩት በኅብለበራኼ ምርምር የአርኤንኤ ፈጠራዎች ክፍል ዳይሬክተርና የሮበርትስ ቤተሰብ (ሮበርትስ ፋምሊ) ተቋም ፕሮፌሰር ናቸው።

በየዓመቱ የሚወጣው የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች እወጃ የሚጀመረው በሕክምና ዘርፍ ሲሆን እስከ መስከረም 28 ባሉት ቀኖች በየዕለቱ በፊዚክስ፣ በኬሚስትሪ፣ በሥነ ፅሁፍ፣ በሰላም እና በምጣኔኃብት ምርምር መስኮች በየዕለቱ አንድ ሽልማት ይታወጃል።

የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ስዊድናዊ ነጋዴ አልፍረድ ኖቤል ዳይናማይት ፈንጂን ፈጥሮ ብዙ ሃብት አግኝቷል።

ኖቤል ከሞተ ከአምስት ዓመታት በኋላ በስሙ የወጣው ሽልማት በ1894 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰጥቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG