በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሯ የኖቤል የኢኮኖሚ ዘርፍ ተሸላሚ ኾኑ


በአሜሪካ የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፈሰር ክላውዲያ ጎልዲን
በአሜሪካ የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፈሰር ክላውዲያ ጎልዲን

በአሜሪካ የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፈሰር ክላውዲያ ጎልዲን፣ የዘንድሮ የኖቤል የኢኮኖሚ ዘርፍ ሽልማት አሸናፊ ኾነዋል።

ፕሮፌሰሯ፤ በዓለም ዙሪያ፣ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ያነሰ ሥራ የማግኘት ዕድል እንዳላቸው፣ ቢያገኙም ክፍያው በአንጻራዊነት ዝቅተኛ እንደኾነ በሚያሳየው ጥናታቸው አማካይነት፣ ሽልማቱን ሊያገኙ እንደቻሉ ታውቋል።

ጥናታቸውን ለማድረግ የ200 ዓመታት የሥራ ገበያ መረጃን የተጠቀሙት ክላውዲያ፣ ከዓለም ሴቶች ግማሽ ያህሉ ብቻ ሥራ እንዳላቸው፣ በአንጻሩ 80 በመቶ ያህሉ ወንዶች ሥራ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ብዙ ጊዜ፣ ክፍት የሥራ ቦታዎች፣ ለተገቢው እና ብቁ አመልካች እንደማይሰጡ የገለጹት ተሸላሚዋ ፕሮፌሰር ክላውዲያ፣ ሴቶች፥ አንድም አይወዳደሩም፤ ቢወዳደሩም ተቀባይነት እንደማያገኙ በጥናታቸው አመልክተዋል።

እስከ አሁን፣ በኢኮኖሚ መስክ የኖቤል ተሸላሚዎች 93 ደርሰዋል፡፡ ከዚኽ ውስጥ ሴቶቹ፣ ክላውዲያ ጎልዲንን ጨምሮ ሦስት ብቻ እንደኾኑ ታውቋል። ፕሮፌሰር ክላውዲያ ግን፣ ከሦስቱ ሴት አሸናፊዎች ውስጥ፣ ሽልማቱን ለብቻ በመውሰዳቸው የመጀመሪያዪቱ ሴት ኾነዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG