በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኖትር ዳም ቃጠሎ


ፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ እምብርት ላይ የሚገኘው ትናንት ከባድ ቃጠሎ የደረሰበት ድንቁ ኖትር ዳም ካቴድራል ግንቡንና በውስጡ የሚገኙትን ዋና ዋናዎቹን የጥበብ ሥራዎች ለማትረፍ መቻሉን የከተማዪቱ የእሳት አደጋ ብሪጌድ አስታወቀ።

በካቴድራሉ ላይ መጠነሰፊ ጉዳት ያደረሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት አራት መቶ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ከዘጠኝ ሰዓት በላይ ታግለዋል።

በምዕራባዊያን ክርስትያን ዘንድ በያዝው የሕማማት ሰሞንና በሣምንቱ ውስጥ ለሚውሉትም ፀሎተ-ሃሙስ፣ የስቅለትና የትንሣዔ ቀናት ቅዳሴ ይካሄድበት በነበረው ካቴድራል ላይ ስለደረሰው ጉዳት ኀዘን ላይ ያሉት የፓሪስ ነዋሪዎች እንዲሁም ሌሎችም የዕድሜ ጠገቡና የታሪካዊው ህንፃ አድናቂዎች አንዱ ሌላውን እያፅናኑ መሆናቸው ተዘግቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG