በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ሰዎች ተገደሉ


ትናንት እሁድ ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ በሚገኝ ሆቴል ላይ በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር አስራ አምስት ደረሰ። ቢያንስ ሃያ ሰዎች መቁሰላቸውን የሞቃዲሾ ፖሊስ ቃል አቀባይ እና የህክምና ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

ከሞቱት መካከል አራቱ አጥቂዎቹ መሆናቸውን ነው የሶማሊያ የጸጥታ ባለሥልጣናት ያስታወቁት።

ጽንፈኛ ታጣቂው ቡድን አልሻባብ ለጥቃቱ ሃላፊነት ወስዷል። ከሞቃዲሾ ታዋቂ ሆቴሎች አንዱ በሆነው አፍሪካ ሆቴል መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ከፈነዳ በኋላ የአልሻባብ ታጣቂዎች የመንግሥቱን የጦር ሰራዊት መለዮ ልብስ ለብሰው በመግባት በከፈቱት ተኩስ ከተገደሉት መካከል አንዱ ጡረታ ላይ ያሉ ጀነራል እና ከውጭ ሃገር የጫጉላ ጊዜያቸውን ለማሳለፍ ወደሞቃዲሾ የሄዱ ሙሽሮች እንደሚገኙበት ታውቋል።

XS
SM
MD
LG