በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግድቡና በዙሪያው ያሉ ጥያቄዎች


የኅዳሴ ግድብ ንድፍየኅዳሴ ግድብ ንድፍ
የኅዳሴ ግድብ ንድፍየኅዳሴ ግድብ ንድፍ

ዓባይ ሊገደብ የመሆኑ ነገር የሰሞኑ የጋለ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ግለቱ ሃገራዊ ብቻ ሣይሆን በተለይ በምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ አካባቢ ላይ ከፍተኛ አንድምታ ያለው ነው፡፡

በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ በየነን በዚሁ ጉዳይ ላይ አወያይቻቸዋለሁ፡፡

አቶ ተፈራ ባነጋገርኳቸው ጊዜ ምዕራብ አፍሪካ ኒዠር ውስጥ ነበሩ፡፡ ወደዚያ የተጓዙት በኒዠር ወንዝ ባለሥልጣንና በአባይ ተፋሰስ ሃገሮች ትብብር መካከል የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ያለ በመሆኑ በዚያ ላይ ለመገኘት መሆኑን ነግረውኝ ነበር፡፡

ስለአባይ ተፋሰስ ሃገሮች ትብብርና ስለስምምነታቸው፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የግድቡን ሥራ መጀመር ያለውን ዓለምአቀፍ አንድምታ አንስተዋል፡፡ ስለኢንቨስትመንቱ፣ ስለቻይና፣ እሥራኤልና ኤርትራ፣ ሊነሱ ስለሚችሉ ሰዎችና የተፈጥሮ አካባቢ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ውስጥ የግድቡ በስም አለመጠቀስን ጉዳይ በሚመለከቱ ሃሣቦች ላይ ይናገራሉ፡፡

ውይይቱን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG