በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ዉሃ ሃብት ሚኒስትር አቶ አስፋዉ ድንጋሞ ስለአባይ ወንዝ አጠቃቀም ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ገለጹ


ሁሉም አገሮች ዉሃዉን በፍትሃዊና መልክ መጠቀም አለባቸዉ

የኢትዮጵያ የዉሃ ሃብት ሚኒስትር አቶ አስፋዉ ዲንጋሞ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ”ለጥያቄዎ መልስ” ዝግጅት ላይ ለአድማጮች ጥያቄ በሰጡት መልስ በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ በቅርቡ እንደገና ስለተፈጠረዉ ዉዝግብ አስረድተዋል።

አቶ አስፋዉ፣ ባለፈዉ ሃምሌ 5 በዋሽንግተን ዲስ ሰልፍ ያደረጉ ኢትዮጵያዉያን የኢትዮጵያ መንግስት በወንዙ አጠቋቀም ላይ ያለዉን አቋም የደገፉና የሌሎችንም አገሮች ድጋፉ የጠየቁ በመሆኑ ተገቢ እርምጃ የወሰዱ ናቸዉ ብለዋል።

ባለፉት አስርና አስራ ሁለት ዓመታት፣ የአባይ ወንዝ ተጠቃሚ አገሮች Nile Basin Initiative የተባለ ፕሮግራም ቀርጸዉ በዚህ ፕሮግራም ዙሪያ ዓለም አቀፍ ህግን በተመለከተ መልኩ ወንዙን ለመጠቀም ድርድር ሲያደርጉ ቆይተዋል፥ ከእንዚህ መካከል አንድዋም ኢትዮጵያ ነች ብለዋል። የድርድሩም ይዘት ዉሃዉን ሁሉም አገሮች በፍትዊ መልክ መጠቀም እናለባቸዉና፣ ለሁለት አገሮች ማለትም ለግብጽና የሱዳን ሞኖፖሊ የስጠዉ በቂኝ ዘመን የተፈረመ ዉል እንዲፈር የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

የአባይ ወንዝ በአስር አገሮች የሚዋሰን መሆኑን ጠቅሰዉ፣ ከአሰሩ የNile Basin Initiative ዘጠኝ ናቸዉ ዘጠኙ ሙሉ ፊርማ ፈርመዉ የሚንቀሳቀሱ ናቸዉ ብለዋል።

አብዛኞቹ አገሮች ባለፈዉ ግንቦት 7, 2002 ኡጋንዳ ከተማ ኢንቴቤ ዉሉን መፈራረማቸዉን ገልጸዋል አቶ አስፋዉ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG