በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአባዩ ሕዳሴ ግድብና በዙሪያው ያሉ ንግግሮች


አባይ
አባይ

`ለጥያቄዎ መልስ` በዚህ በሰሞኑ ዝግጅት አወያይ እና አወዛጋቢ በሆነው "ታላቁ የሕዳሴ ግድብ" ተብሎ በተሰየመው የአባይ ግድብ ላይ አተኩሯል፡፡

"አባይ መገደብ አለበት" በሚለው ሃሣብ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይስማማል፡፡ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት የግድቡ ግንባታ አሁን በድንገት በኢትዮጵያ መንግሥት መነሣቱና እነርሱን ያገለለ የገዥው ፓርቲና ደጋፊዎቹ ብቻ ፕሮዤ ሆኖ መታየቱ፣ ግድቡ በዓይነቱ ግዙፍ መሆኑና የሚያስፈልገው ወጭ ከፍተኛነት፣ ለዚህም ሕዝብ `ቦንድ ግዛ` መባሉ እያወያየ ነው፡፡

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና ደጋፊዎቹ `ግድቡ ኢትዮጵያን ከድኅነት ያላቅቃል፣ የግንባታው ሃሣብም አዲስ አይደለም፤ ውሎ ያደረ ነው፤ ድጋፍ ይገባዋል` ይላሉ፡፡

የሕዳሴ ግድብ ሥራን በተመለከተ ስለዕቅዱ ዓላማና ወቅታዊነት፣ ቴክኒካዊ አሠራሩን፣ ግንባታው ስለሚጠይቀው ወጪ፣ ከአጎራባች አገሮች በተለይም ከናይል ተፋሰስ አገሮች ጋር ባለው ግንኙነት ላይ የሚኖረው አንድምታ፣ ዕቅዱ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚዎችንና ሕዝብን ሰለማሣተፉ እና ሌሎችም ጥያቄዎች ደረሰውናል።

በእነዚህ ነጥቦች ዙሪያ የአድማጮቻችንን ጥያቄ እንዲመልሱልን ሁለት እንግዶችን ጋብዘናል፡፡

ኢንጂነር ሰሎሞን ገብረሥላሴ በዩናይትድ ስቴትሷ ካሊፎርኒያ ግዛት በመንግሥት ውኃ ልማት ክፍል በምሕንድስና ክፍል ያገለግላሉ። በግድቡ መሠራት ላይ ተቃውሞ ባይኖራቸውም ከተቃዋሚዎች ወገን የሚሠነዘሩ ጥያቄዎችን በመተንተን መልስ ይሰጣሉ።

አቶ ብርሃኑ ዳምጤ ደግሞ በኦሃዮ ግዛት የኢትዮጵያ ሲቪሊቲ ፎረም የተወሰነ የውይይት መድረክ የሚያስተናግዱና የኢትዮጵያ መንግሥት ደጋፊዎች አስተባባሪ ናቸው።

ሁለቱ ለአድማጮቻችን ጥያቄዎች የሰጧቸውን መልሶች ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG