በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለቦኮ ሃራም ቡድን ድጋፍ በማድረግ የተከሰሱ ቅጣት ተወሰነባቸው


የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ ለናይጄሪያው ሽብርተኛ ቡድን ለቦኮ ሃራም የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የተከሰሱ ስድስት ናይጄሪያውያን ከአስር ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የሚደርስ ቅጣት ተወሰነባቸው።

ዲይሊ ትረስት የተባለው ጋዜጣ ባወጣው ሪፖርት ከሦስት ዓመታት በፊት የታሰሩት ተከሳሾቹ ባለፈው ዓመት ቅጣቱ ተፈርዶባቸው የነበረ ሲሆን ይግባኝ ፍርድ ቤት ቅጣቱን አጽንቶታል።

ሰዎቹ እኤአ ከ2015 - 2016 በነበረው ጊዜ ውስጥ ለቦኮሃራም የሚውል ሰባት መቶ ሰማኒያ ሺህ ዶላር ከዱባይ ወደ ናይጄሪያ ልከዋል ተብለው ተወንጅለዋል።

XS
SM
MD
LG