በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጀሪያ ጦር ኃይል በቦኮ ሃራም ተጠልፈው ከነበሩ ልጃገረዶች አንዷን አስለቀቀ

የናይጀሪያ ጦር ኃይል፣ በአማፂው ቡድን ቦኮ ሃራም ከአራት ዓመታት በፊት ከቺቦክ ትምህርት ቤት ተጠልፈው ከነበሩት ልጃገረዶች መካከል አንዷን ማስለቀቁ ተገለፀ።

የናይጀሪያ ጦር ኃይል፣ በአማፂው ቡድን ቦኮ ሃራም ከአራት ዓመታት በፊት ከቺቦክ ትምህርት ቤት ተጠልፈው ከነበሩት ልጃገረዶች መካከል አንዷን ማስለቀቁ ተገለፀ።

ጦር ኃይሉ ዛሬ በትዊተር መልዕክቱ እንዳስታወቀው፣ ወታደሮቹ ከሰሜናዊቷ ምሥራቅ ፑለካ ከተማ ያስለቀቁት፣ ሳሎሚ ፓጉ የተባለችዋን ልጃገረድ ነው።

ባለሥልጣናትም፣ ፓጉ በቦኮ ሃራም ከተጠለፉት የቺቦክ ልጃገረዶች አንዷ ነች ሲሉ አረጋግጠዋል።

ቦኮ ሀራም ጠልፎ ያገታቸው 270 ልጀረዶች ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ወዲያውኑ ሲያመልጡ አሁንም ግን ወደ 219 የሚሆኑቱ በእስላማዊው ነውጠኛ ቡድን ቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ ነው የተገለጠው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG