በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ ታጣቂዎች ያገቷቸውን ተማሪዎች ለቀቋቸው


የናይጄሪያ ታጣቂዎች ባለፈው ግንቦት ወር ኒጀር በተሰኘች ከተማ ከሚገኝ እስላማዊ ትምህርት ቤት ካገቷቸው ተማሪዎች ውስጥ ጥቂቶቹን ለቀዋቸዋል።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አልሀሰን አቡባከር እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን የለቀቋቸው ባለፈው ሀሙስ ባቅራቢያው በምትገኘው ካዱና ከተማ ነው።

ተማሪዎቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ከመመለሳቸው በፊት ከናይጄሪያ ባለስልጣናት ጋር የሚገናኙ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው ልጆቹ እንዲፈቱ ሁለት ግዜ የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለዋል።

ታጣቂዎቹ በግንቦት መጨረሻ ላይ ትምህርት ቤቱን ከበው 136 ተማሪዎቹን መጥለፋቸው ይታወሳል። ከነዚህ ውስጥ ስድስቱ በዕገታው ላይ እንዳሉ ህይወታቸው ሲያልፍ 15ቱ ጠፍተው አምልጠዋል።

XS
SM
MD
LG