በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ መንግሥት ሠራተኞች እና የማህበር አባላት በዋጋ ንረት ምክንያት የሥራ ማቆም አድማ ጀመሩ


የናይጄሪያ መንግስት ሠራተኞች እና የሠራተኛ ማህበራት የተቃውሞ ሰልፍ፣ በሌጎስ፣ ናይጄሪያ፣ እአአ የካቲት 27/2024
የናይጄሪያ መንግስት ሠራተኞች እና የሠራተኛ ማህበራት የተቃውሞ ሰልፍ፣ በሌጎስ፣ ናይጄሪያ፣ እአአ የካቲት 27/2024

የናይጄሪያ መንግስት ሠራተኞች እና የሠራተኛ ማህበራት ከማክሰኞ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ጀምረዋል። በርካታ ሰዎች በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና እየጨመረ በመጣው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ቁጣ ላይ ባሉበት ወቅት የተጀመረው አድማ ቁልፍ የመንግስት አገልግሎቶችን ሊያቋርጥ እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል።

በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ በሆነችው አገር ባለፈው አመት ሥልጣን የተረከቡት ፕሬዝዳንት ቦላ ቲናቡ፣ ለነዳጅ ይደረጉ የነበሩ ድጎማዎችን ማቆም እና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ማዋሃድን የሚያካትቱ ፖሊሲዎችን ያውጡ ሲሆን፣ ይህም ናይራ ከዶላር አንፃር የነበረው ዋጋ እንዲቀንስ አድርጓል።

የቤንዚን ዋጋ ከእጥፍ በላይ የጨመረ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት የጨምረው የዋጋ ግሽበት ባለፉት ሦስት አስርት አመታት ባልታየ ሁኔታ ባለፈው ወር ወደ 30 ከመቶ መድረሱን የብሔራዊው ስታቲስቲክስ ቢሮ መረጃ ያሳያል።

በአድማው የተሳተፉት የናይጄሪያ የሠራተኞች ኮንግረስ ፕሬዝዳንት ጆ አጃኢሮ "ረሃብ ላይ ነን። ይህንን የማይረዳ ማንም የለም" ሲሉ ተናግረዋል። ሌሎች ተሳታፊዎችም አድማው የመንግስትን ትኩረት ማግኘት የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል።

"ነገሮች ከእጃችን እያመለጡ ነው" ያለው በዋና ከተማዋ አቡጃ የሱቅ ባለቤት የሆነው ክሪስቲያን ኦሜጄ በበኩሉ "የዋጋ ማሻቀቡ ቀጥሏል፣ መንግስት ግን አደርገዋለሁ የሚለውን እርዳታ አላቀረበም" ሲል አስተያየት ሰጥቷል።

ይህ አድማ በናይጄሪያ ከተካሄዱ አድማዎች አዲስ የተቀሰቀሰው ሲሆን፣ በጥቅምት ወር የተደረገውን አድማ ለማስቆም፣ ወርሃዊ ክፍያዎች እና ድጎማ ለማድረግ በሠራተኛ ማህበራት እና መንግስት መካከል ስምምነት ተደርሶ ነበር።

ማህበራቱ መንግስት ለስድስት ወራት በየወሩ የ20 ዶላር ደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ እና በሚሊየን ለሚቆጠሩ ለተጋላጭ ሰራተኞች፣ ለሦስት ወራት ያክል የ15 ዶላር ድጋፍ ለማድረግ የገባውን ቃል ማክበር አልቻለም ብለዋል።

ባለፈው አመት በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ አውቶቡሶችን ለጅምላ መጓጓዣነት ለማሰማራት የተገባው ቃልም ተግባራዊ ሊሆን አልቻለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG