በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያው የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሃላፊ ታገዱ


የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ
የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ

የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ የአገሪቱን የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኃላፊ ከሥራ አግደዋል። ውሳኔው ሥልጣንን ካለ አግባብ ተጠቅሟል በሚል በኮሚሽኑ ላይ በመደረግ ላይ ያለው ምርመራ አካል ነው ተብሏል።

የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ወንጀሎች ጉዳይ ኮሚሽን ሃላፊው አብዱልራሺድ ባዋ ከታገዱ በኋላ የአገሪቱ የጸጥታ አገልግሎት ቢሮ እንዳነጋገራቸውም ታውቋል።

የፕሬዚዳንትነት ሥልጣኑን ከጨበጡ ሁለት ሳምንት የሆናቸው ቦላ ቲኑቡ፣ እስከ አሁን ሁለት ባለሥልጣናትን ከሥልጣን አግደዋል።

ቦላ ቲኑቡ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አደርጋለሁ ብለው ቃል በመግባት በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው አሸንፈው ስልጣኑን ተቆጣጥረዋል።

መንግሥት ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ኃላፊው ከሥራቸው የታገዱት ኮሚሽኑ ሥልጣኑን ካለ አግባብ እየተጠቀመ ነው የሚል ከበድ ያለ ክስ እየቀረበበት በመሆኑ ነው ብሏል።

ባለፈው ሳምንት ቦላ ቲኑቡ የማዕከላዊ ባንክ ገዢው ጋድዊን ኢሜፊሌን ካገዱ በኋላ፣ የጸጥታ ክፍሉ በቁጥጥር ሥር አውሏቸዋል።

XS
SM
MD
LG