በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ የወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማነቆዎች ለማስወገድ ጥረት እየተደረገ ነው


በናይጄሪያ የወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማነቆዎች ለማስወገድ ጥረት እየተደረገ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00

በናይጄሪያ የወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማነቆዎች ለማስወገድ ጥረት እየተደረገ ነው

በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ የሀገራትን የሕዝብ ቁጥር እና የምጣኔ ሀብት ይዞታ እንደሚከታተለው ዎርልዶሜትር ስሌት፣ 207 ሚሊዮን ከሚጠጋው የናይጄሪያ ሕዝብ ውስጥ 70 በመቶው ወጣት ነው። ይህም ናይጄሪያን በወጣቶቿ ቁጥር በዓለም ከቀዳሚዎቹ ተርታ ያሰልፋታል፡፡

ይኹንና እምብዛም ተቀባይነት ባላገኙት ሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፉክክሩ ተሳትፎ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመኾኑ፣ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የወጣቶች ውክልናና የሚሰጣቸው ስፍራ ዝቅተኛ ኾኖ ቆይቷል።

አንዳንድ በወጣቶች የሚመሩ ተቋማት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ታዲያ፣ ይህን ኹኔታ ለመለወጥ በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ድርጅቶቹ፥ ለሌሎች ብቻ የተመደቡ የሚመስሉትን የኃላፊነት መቀመጫዎች በመጠየቅና አንድ ሰው ዕጩ ኾኖ በሚቀርብበት ወቅት የሚሞላውን ቅጽ ለማግኘት የሚወጣውን ወጪ በመገምገም ኹኔታውን ለመለወጥ እየሞከሩ ናቸው።

ቲሞቲ ኦቢዙ ከአቡጃ ያደርሰንን ዘገባ፣ አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG