ማዕከላዊ ናይጄሪያ ውስጥ ሸማቂዎች ባለፈው እሁድ አመሻሽ ላይ ባደረሱት ጥቃት፣ 26 የጸጥታ ሰራተኞችን ገድለው ሌሎች ስምንት ማቁሰላቸውን ሁለት ወታደራዊ ምንጮች ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።
በተያያዘ፤ አንድ የአየር ኃይል ቃል አቀባይ በሰጡት ቃል፣ ሰኞ ማለዳ ላይ የቆሰሉ አባላትን ለመታደግ፣ ሠራዊቱ ከወንጀለኛ ቡድኖች ጋር እየተዋጋ ወደነበረበት አካባቢ የተሰማራች ሄሊኮፕተር መከስከሷን ተናግረዋል።
የሄሊኮፕተሯ ሰራተኞቹ እና ተሳፋሪዎች በሕይወት ይትረፉ አይትረፉ ግን ቃል አቀባዩ አላስረዱም።
መረጃ የመስጠት ፍቃድ ስሌላቸው ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት ሁለቱ የጦር መኮንኖች በበኩላቸው፣ በጥቃቱ የተገደሉትን 11 ወታደሮች አስከሬን እና ሰባት የቆሰሉ ወታደሮችን አሳፍራ ከተነሳችው የአየር ኃይል ሄሊኮፕተር ጋር የነበረው ግንኙነት መቋረጡን እና ዘግይቶም በሸማቂዎቹ በተተኮሰ መሳሪያ ተመታ መከስከሷ መረጋገጡን አስረድተዋል። አያይዘውም ጥቃቱን የፈጸሙት “ወንጀለኛ” ያሉት ቡድን አባላት በተኩስ ልውውጡ ብርቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
መድረክ / ፎረም