በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ ሠራተኛ ማኅበር የሥራ ማቆም አድማውን ለአንድ ሳምንት አቆመ


የናይጄሪያ የሠራተኛ ማኅበራት ፕሬዚዳንት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪን በመቃወም የተደረገ ሰልፍ፣ ሌጎስ፣ ናይጄሪያ
የናይጄሪያ የሠራተኛ ማኅበራት ፕሬዚዳንት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪን በመቃወም የተደረገ ሰልፍ፣ ሌጎስ፣ ናይጄሪያ

ዋናዎቹ የናይጄሪያ የሠራተኛ ማኅበራት የሥራ ማቆም አድማቸውን ዛሬ ለአንድ ሳምንት አቋርጠዋል። ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቀጥል የታቀደውን የሥራ ማቆም አድማ ለማቋረጥ የወሰኑት ከመንግሥቱ ጋራ ስለ አዲስ የሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ለሚደረገው ድርድር ጊዜ ለመስጠት በሚል መሆኑን አመልክተዋል።

የናይጄሪያ መንግሥት የወሰዳቸው የለውጥ እርምጃዎች ያስከተሉት የኑሮ ውድነት መናር ቀውሱን አባብሶታል።

ሁለቱ ትላልቆቹ የናይጄሪያ የሠራተኛ ማኅበራት፣ የጀመሩት የሥራ ማቆም አድማ አገር አቀፍ የኅይል ማመንጫዎችን ያስቆሙ ሲሆን በረራዎችንም አስተጓጉለዋል።

ሠራተኛ ማኅበራቱ ትላንት ማታ ከመንግሥቱ ጋራ የተነጋገሩ ሲሆን መንግሥት ያቀረበውን 41 ዶላር ከ38 ሳንቲም የሠራተኞች ዝቅተኛ የወር ደመወዝ ክፍያ ከፍ ለማድረግ መስማማቱ ተነግሯል። በምን ያህል ከፍ እንደሚያደርግ ግን አልተገለጠም።

የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ቦላ ቲኑቡ የናዳጅ ዋጋውን እንዳያጨምር አድርጎ የቆየውን ድጎማ ለማንሳት የወሰዱትን እርምጃ እንዲቀለብሱ ጫናው በርትቶ ቀጥሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG