በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

​በናይጄሪያ የት/ቤት ሕንጻ ተደርምሶ 16 ተማሪዎች ሞቱ

በማዕከላዊ ናይጄሪያ የአንድ ት/ቤት  ሕንፃ ተደርምሶ በውስጡ ፈተና በመውሰድ ላይ ከነበሩት ተማሪዎች መካከል 16 የሚሆኑት መሞታቸው ታውቋል።
በማዕከላዊ ናይጄሪያ የአንድ ት/ቤት  ሕንፃ ተደርምሶ በውስጡ ፈተና በመውሰድ ላይ ከነበሩት ተማሪዎች መካከል 16 የሚሆኑት መሞታቸው ታውቋል።

በማዕከላዊ ናይጄሪያ የአንድ ት/ቤት ሕንፃ ተደርምሶ በውስጡ ፈተና በመውሰድ ላይ ከነበሩት ተማሪዎች መካከል 16 የሚሆኑት መሞታቸው ታውቋል።

በፈረሰው ሕንጻ ሥር የነበሩ ተማሪዎች ለዕርዳታ ሲጮሁ የተሰሙ ሲሆን የዕርዳታ ሠራተኞች ሕፃናቱን ለማውጣት ሲጥሩና ወላጆችም በተስፋ መቁረጥ ሁኔታውን ሲከታተሉ ተስተውሏል።

ባለሥልጣናት በአደጋው የሞቱትን ሕፃናት “በርካታ” በማለት ሲገልጹ፣ በሥፍራው የነበረው የኤኤፍፒ ዘጋቢ ዘጠኝ አስከሬኖች ከፍርስራሹ ሲወጡ ማየቱን ገልጿል። በአስከሬን ማቆያዎች አስራ አንድ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሱ ሕጻናት አስከሬኖችን መቁጠሩንም አስታውቋል።

በአካባቢው የሚኖር አንድ ግለሰብም 8 አስከሬኖች ከፍርስራሹ ሲወጡ መመልከቱን ተናግሯል። በአካባቢው የሚገኝ ሆስፒታል የተጎዱ 15 ተማሪዎችን መቀበሉን አስታውቋል።

ለሕንጻው መደርመስ ምክንያቱ ወዲያው ባይታወቅም፣ አደጋው የተከሰተው በአካባቢው ለሦስት ቀናት የጣለውን ዝናብ ተከትሎ መሆኑ ታውቋል።

በናይጄሪያ የሕንፃ መደርመስ በተደጋጋሚ የሚስተዋል ሲሆን፣ ምክንያቱ ደግሞ ጉቦ የግንባታ ደንብ ተፈጻሚነትን በማላላቱ፣ ደረጃውን ያልጠበቀ የሕንፃ ግብዓትና አሠራር እንደሆነ ተነግሯል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ 55 ሰዎች በሕንፃ መደርመስ አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

እአአ ከ2021 ወዲህ ሌጎስ ውስጥ 152 ሕንፃዎች ተደርምሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG