በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጀርያ የረድኤት ሰራተኛ መገደሏ ተጠቆመ


ናይጀርያ ውስጥ በያዝነው ዓመት ቀደም ሲል በፅንፈኛ ሙስሊም ቡድን ተጠልፋ የነበረችው ሁለተኛ የረድኤት ሰራተኛ መገደሏን የናይጀርያ መንግሥት ገልጿል።

ናይጀርያ ውስጥ በያዝነው ዓመት ቀደም ሲል በፅንፈኛ ሙስሊም ቡድን ተጠልፋ የነበረችው ሁለተኛ የረድኤት ሰራተኛ መገደሏን የናይጀርያ መንግሥት ገልጿል።

በጽንፈኛው ቡድን የተገደለችው ሀዋ ሞሐመድ ሊማን እንደምትባል የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ተናግሯል። በዓለምቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሚረዳ ሆስፒታል ትሰራ እንደነበር ተገልጿል።

ሌላዋ በቀይ መስቀል ኮሚቴ ትሰራ የነበረችው ሳይፉራ ኾርሳና ሊማን ባለፈው ግንቦት ወር ነበር የተጠለፉች።

ፅንፈኛው ቡድን በቦርኖ ክፍለ ሀገር ራን በተባለችው ከተማ ላይ ባለፈው መጋቢት ወር ወረራ ባካሄደበት ወቅት ነበር ሁለቱ ሰራተኞች የተጠለፉት። አሊስ ሎክሻ የተባለች የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ሰራተኛ ነርስም አብራ ተይዛለች።

ፅንፈኛው ቡድን ኾርሳን ባለፈው ወር ገድሎ መንግሥት እስከ መጪው ሰኞ ጥያቄውን ካላሞላ በስተቀር ከሁለቱም ሴቶች አንዷን እንደሚገድል ባስታላለፈው ቪድዮ ዝቶ ነበር፣ ጥያቄው ምን እንደሆነ አለተገለፀም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG