በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ የመብቶች ቡድን ሠራዊቱን መመርመር ጀመረ


ፎቶ ፋይል፦ አቡጃ፤ ናይጄሪያ
ፎቶ ፋይል፦ አቡጃ፤ ናይጄሪያ

በናይጄሪያ የተቋቋመው ልዩ የሰብአዊ መብቶች መርማሪ አካል፣ “ሠራዊቱ እስላማዊ አማጽያንን ለመከላከል በሚደረገው ዘመቻ ህጻናትን ገድሏል፣ በድብቅ አስገዳጅ የጽንስ ማቋረጥ መርሃ ግብሮችንም ያካሂዳል” ሲል ትናንት ማክሰኞ የወጣውን የሮይተርስ ዘገባ እያጣራ መሆኑ ተዘገበ፡፡

ሮይተርስ ዛሬ ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው መርማሪው አካል የመብት ጥሰቶችን በመፈጸም ጥፋተኛ ሆኖ ያገኛቸውን ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚመራቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡

የናይጄሪያ ጦር ሁልጊዜም የሚወጡ ዘገባዎችን የሚያስተባባል መሆኑን ሮይተርስ የዘገበ ሲሆን፣ ባላፈው ታህሳስም ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣውን ዘገባ፣ እውነት አይደለም በሚል፣ የራሱን የማጣራት ሂደት እንደማያደርግ ማስታወቁን ገልጿል፡፡

በመንግሥት የተመደበው የናይጄሪያ ብሄራዊ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አንቶኒ ኦጆኩ፣ በጡረታ ላይ በሚገኙት የቀድሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሚመራ ሰባት አባላት ያሉት የመርማሪዎች ቡድን መቋቋሙን ትናንት ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ሮይተርስ ባለፈው ታህሳስ በርካታ የዓይን እማኞችንና ሰነዶችን መሠረት አድርጎ ባወጣው ሪፖርት፣ የናይጄሪያ ጦር፣ ብዙዎቹ በእስላማዊ ሚሊሻዎች ታግተው የተወሰዱ እና የተደፈሩ 10ሺ ነፍሰጡር ሴቶችና ህጻናትን በማስገደድ፣ ጽንስ እንዲያቋርጡ የሚያደርግ መርሃ ግብር ተግባራዊ ማድረጉን ዘግቧል፡፡

አሁንም አንድ ወር ቆይቶ የወጣው ሁለተኛው የሮይተርስ ዘገባ፣ በርካታ የዓይን ምስክሮችን ዋቢ በማድረግ፣ ሠራዊቱ አሸባሪዎች ናቸው ወይም ወደፊት ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ግምት በጦርነቱ መካከል ያገኛቸውን ህጻናት መግደሉን ዘግቧል፡፡

የናይጄሪያ ጦር መሪዎች ጽንስ ማቋረጥ የሚባል መርሃ ግብር የሌለ ሲሆን የሚሞቱ ህጻናትም የግድያ ዒላማ ሆነው አያውቁም ብለዋል፡፡

አጣሪው ቡድን በጥቃቱ ወይም በሰብአዊ መብቱ ጥሰት ለደረሰው ጉዳት ካሳ መከፈል አለመከፈሉን የሚወስን መሆኑም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG