በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ጸጥታ ኃላፊዎቻቸውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ


የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ

የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ ባላፈው ሳምንት በዋና ከተማ አቡጃ የሚገኙ ብዙ የውጭ አገር ሚሲዮኖች ላይ የሽብር ማስጠንቀቂያ መድረሱን ተከትሎ ዛሬ ሰኞ የጦር አዛዦች፣ ከፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ ኃላፊዎች ጋር አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄዱ መሆናቸው ተነገረ፡፡

የቡሃሪ ቃል አቀባይ ጋርባ ሼሁ የዛሬው ስብሰባ እንደሚካሄድ ያስታወቁት ትናንት እሁድ አመሻሹ ላይ ሲሆን የስብሰባው ዓለማ የአገሪቱን ደህንነት መዋቅር ለማጠንክር መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ እንግሊዝ አየርላንድ፣ ካናዳ፣ ጀርመን፣ ቱርክእና አውስትራሊያ ዜጎቻቸው አስፈላጊ ካልሆነ ወደ ናይጄሪያ እንዳይጓዙ አሳስበዋል፡፡

የናይጄሪያ ባለሥልጣናት አገሪቱ ሰላም መሆንዋንና ምንም የሚያሰጋ ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በነዋሪዎች መካከል ፍራቻን የፈጠረው ዛቻ አንዳንድ የንግድና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲዘጉ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡

የናይጄሪያ ጸጥታ ኃይሎች በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ያሉትን የጅሃዲስቶች ቡድኖች እየተዋጉ ሲሆን ቡድኖቹ ወደ ሌላው የአገሪቱ ክፍል እየተስፋፉ አይቀርም የሚለው ስጋት መፍጠሩ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG