በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጀሪያ ተጥሎ የቆየው ዕገዳ ውሳኔ


የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመገደብ ሲባል በናይጀሪያ ተጥሎ የቆየው የመንቀሳቀስ ዕገዳ ቀስ በቀስ መላለት እንደሚጀመር የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ አስታውቀዋል። ገደቡን የማላላት ዕርምጃ በመጭው ሰኞ በመዲናይቱ ሌጎስ አቡጃና ኦጉን ክፍለ ግዛት ይተገበራል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በአለፈው ሰኞ ማታ በሃገሪቱ ቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር፣ ውሳኔ ላይ የደረሱት ከአንድ ወር በላይ የቆየውን ዕገዳ ከገመገሙ በኋላ መሆኑን ገልጸዋል። የቫይረሱን መዛመት እየተቆጣጠሩ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስመዝግበዋል። የሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ እንደሆነ፤ የሰዓት እላፊ ገደብ እንደሚኖር ቡሃሪ አከለዋል።
በሰሜን ምዕራብ ካኖ የቫይረሱ መዛመት በመጨመሩ የመንቀሳቀሱ ዕገዳ እንደሚቀጥል ዕቃዎች፣ የህክምና ሰራተኞች፣ ወደ ቦታው እንደሚላኩ ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል።
በናይጀሪያ ዛሬ 1ሺህ 532 የኮሮና በሽተኞች እንዳሏት 44 እንደሞቱባት ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG