በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ “ማርሽ ቀያሪ" ያለችውን ባለቢሊዮን ዶላር ጥልቅ የባህር ወደብ አስመረቀች


አዲሱ የሌኪ ጥልቅ ባህር ወደብ
አዲሱ የሌኪ ጥልቅ ባህር ወደብ

ናይጄሪያ በቻይና የተገነባውን እና በቢሊየን ዶላር የሚገመት ወጪ የወጣበትን ጥልቅ ወደብ ትናንት ሰኞ ሌጎስ ላይ አስመርቃ ሥራ አስጀምራለች። ይህም በአገሪቱ ወደቦች ላይ ያለውን መጨናነቅ በማቃለል እና ወደ ሌሎች መዳረሻዎች የሚጓጓዙ እቃዎችን በማስተናገድ ናይጄሪያን የአህጉሩ የመጓጓዣ ማዕከል ለማድረግ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የመሰረተ ልማት ግንባታን የመንግሥታቸው የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ቁልፍ ምሰሶ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ያሁኑም ጥረታቸው ፓርቲያቸው በሚቀጥለው ወር በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲያሸንፍ ይረዳዋል የሚል ተስፋ አሳድረዋል።

አዲሱ የሌኪ ጥልቅ ባህር ወደብ ሰባ አምስት በመቶ በቻይናው የሃርበር ኢንጂነሪንግ ኩባንያ እና በቶላራም ግሩፕ ባለቤትነት የተያዘ ሲሆን፣ የቀረው የሌጎስ የግዛት አስተዳደር እና የናይጄሪያ የወደቦች ባለሥልጣን ድርሻ ነው።

ፕሬዚዳንት ቡሃሪ ወደቡን መርቀው ከከፈቱ በኋላ የተናገሩት በናይጄሪያ የቻይና አምባሳደር ኩይ ጂያንቹን ለሮይተርስ ሲናገሩ "ይህ

መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ፕሮጄክት፣ ማርሽ ቀያሪ ፕሮጀክት ነው። በትንሹም ለ200, 000 ሰዎች ሥራ መፍጠር ይችላል።" ብለዋል።

ቻይና በሁለትዮሽ በሚደረግ ብድር ከትልልቆቹ የናይጄሪያ አበዳሪዎች አንዷ ስትሆን፣ የባቡር፣ የመንገድ ሥራ እና የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ታላላቅ የግንባታ ሥራዎች በገንዘብ መደገፏ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG