በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተሟጋቾች ናይጄሪያ የሼልን የነዳጅ ሽያጭ ዕቅድ እንዳትቀበል አሳሰቡ


ተሟጋቾች ናይጄሪያ የሼልን የነዳጅ ሽያጭ ዕቅድ እንዳትቀበል አሳሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:18 0:00

ተሟጋቾች ናይጄሪያ የሼልን የነዳጅ ሽያጭ ዕቅድ እንዳትቀበል አሳሰቡ

የአካባቢ እና የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ የናይጄሪያ መንግሥት፣ ከግዙፍ የነዳጅ ኢንዱስትሪው የሚመነጨውን የከባቢ ብክለት ለመቋቋም የበለጠ ጥረት ካላደረገ በቀር፣ ሼል ሥራውን ለኒጀር ዴልታ ለመሸጥ ያሰበውን ዕቅድ እንዲገታ እየጠየቁ ነው፡፡

እንደ ሼል ያሉ የኀይል ማመንጫዎች፣ ለዐሥርት ዓመታት፣ ከናይጄሪያው ኒጀር ዴልታ የነዳጅ ዘይት አውጥተዋል። ይህ ለኩባንያዎቹ እና ለናይጄሪያ መንግሥት፣ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አስገኝቷል፡፡ ነዋሪዎች ግን ከፍተኛ የከባቢ ጉዳት ያስከተለ መኾኑን ሲገልጹ ቆይተዋል።

ፍሎረንስ ካዬምባ፣ በኒጀር ዴልታ ውስጥ በናይጄሪያ በፖርት ሃርኮርት የሚገኘው ስቴክሆልደርስ ዴሞክራሲ ኔትዎርክ የተባለ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድን ዲሬክተር፣ "ሰብል ማብቀል አትችልም፤ ውኃውን መጠጣት አትችልም፤ ዓሣ ማጥመድ አትችልም፤ ምክንያቱም ዓሦቹ እየሞቱ ነው ወይም ሞተዋል፤” ሲሉ ያደረሰው ጉዳት ያስረዳሉ፡፡

ሼል፣ ባለፈው ጥር ወር፣ ከኒጀር ዴልታ እየወጣ መኾኑን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው፣ የናይጄሪያን ቅርንጫፍ የማዕድን ፈቃዶችንና መሠረተ ልማቶችን፣ በዋናነት በሀገር ውስጥ ለሚገኙ አምስት ኩባንያዎች ጥምረት ይሸጣል። ይኸውም ሼል፣ ከነዳጅ ዘይቶች ምርት አቅርቦት ለመወጣት የሚያደርገው የሽግግር ዕቅድ አካል ነው፤ ተብሏል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች፣ ሼል ለቆ ከመውጣቱ በፊት አካባቢውን በማጽዳት የበለጠ መሥራት እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡ የዘርፈ ብዙ ኩባንያዎች ምርምር ማዕከል ወይም በአጭሩ ሶሞ(SOMO) እየተባለው የሚጠራው የኔዘርላንድ ድርጅት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት፣ የሼል አካባቢውን አስተላልፎ በመስጠት የመወጣት ዕቅድ፣ “ጊዜያዊ ፈንጂ ነው” ሲል አስጠንቅቋል።

አሁን ያለንበት ሁኔታ፣ አነስተኛ የነዳጅ ዘይት አጣሪዎች የተከሠተውን ነገር ይበልጥ የሚያጠናክሩበት ነው፤ ያ ብክለት ቀድሞውኑም ነበረ። ስለዚህ እነርሱ ይህን መልቀቅ ሲጀምሩ በጣም ከባድ ይኾናል። ማነው ማንን ተጠያቂ የሚያደርገው?”

ካዬምባ፣ “ሼል ወደ ኋላ ትቶት የሚሔደው የብክለት ውርስ በጣም ያሳስበናል፤” ይላሉ፡፡ ይህ ሼልን ብቻ ሳይኾን፣ ንብረታቸውን ከኒጀር ዴልታ ያወጡ ሌሎች የነዳጅ ኩባንያዎችንም እንደሚጨምር ካዬባም ይናገራሉ። አያይዘውም፣ “ፌደራል መንግሥት እነዚህን ጉዳዮች መመርመሩ በጣም አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ነዳጅ ዘይቱ ለዘለዓለም አይፈስም፤” በማለት አክለዋል፡፡

እንደ ሼል ያሉ የነዳጅ ኩባንያዎች፣ በከባቢ ጥበቃ ቡድኖች ዘንድ አከራካሪ ለኾነው የነዳጅ ዘይት መፍሰስ፣ ብዙውን ጊዜ የስርቆት እና የማጭበርበር ድርጊቶችን በመንሥኤነት ያቀርባሉ፡፡

ፍሎረንስ ካዬምባ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች በአነስተኛ የነዳጅ ማጣሪያዎች በመሰማራት ከጥቂት ምርት ገንዘብ ለማግኘት እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፡፡

"አሁን ያለንበት ሁኔታ፣ አነስተኛ የነዳጅ ዘይት አጣሪዎች የተከሠተውን ነገር ይበልጥ የሚያጠናክሩበት ነው፤ ያ ብክለት ቀድሞውኑም ነበረ። ስለዚህ እነርሱ ይህን መልቀቅ ሲጀምሩ በጣም ከባድ ይኾናል። ማነው ማንን ተጠያቂ የሚያደርገው?” ሲሉ ካዬምባ ጠይቀዋል፡፡

የዘርፈ ብዙ ኩባንያዎች ምርምር ማዕከል በአጭሩ ሶሞ እየተባለው የሚጠራው የኔዘርላንድ ድርጅት፣ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት፣ ሼል ይዞታውን እየሸጠ ያለው፣ ነባሩን መሠረተ ልማት ለመጠቀም ፋይናንስ ወይም ፍላጎት ለሌላቸው የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች እንደኾነ አመልክቷል፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG