በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ ጎርፍ 30 ገድሎ 400ሺሕ አፈናቀለ


በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ማዩዱጉሪ በተባለች ከተማ ከባድ ጎርፍ መኖሪያ ቤቶችን አጥለቅልቋል።
በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ማዩዱጉሪ በተባለች ከተማ ከባድ ጎርፍ መኖሪያ ቤቶችን አጥለቅልቋል።

በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ማዩዱጉሪ በተባለች ከተማ ከባድ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ እስከ አሁን 30 ስዎች መሞታቸው ሲታወቅ፣ 400ሺሕ የሚሆኑትን ደግሞ ከመኖሪያ ቤታቸው አፈናቅሏል።

በአካባቢው የነበረ ግድብ በመሙላቱ፣ ጎርፉ መኖሪያ ቤቶችን አጥለቅልቋል። የከተማዋ 40 በመቶ በውሃ ውስጥ ሰምጦ እንደሚገኝ ባልሥልጣናት አስታውቀዋል።

የተመድ የስደተኞች ወኪል በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ እንዳስታወቀው፣ አደገኛ ጎርፍ ሲከሰት ከ30 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየና አስከፊ አደጋ ያስከተለ ነው ሲል አስታውቋል።

የእስላማዊ ነውጠኞች ሁከት በሚያጠቃት ከተማ ድንገት በጨመረው የጎርፍ መጠን 23ሺሕ ቤቶች ተጥለቅልቀዋል።

በናይጄሪያ የዝናብ ወቅት ከጀመረ ወዲህ ጎርፍ 229 ሰዎችን ሲገድል፣ ከ380ሺሕ በላይ ሰዎችን ደግሞ ከመኖሪያቸው እንዳፈናቀለ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG