በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ 11 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የዝሆን ጥርስ አወደመች


የናይጄሪያ ባለሥልጣናት 2.5 ሜትሪክ ቶን የሚመዝን እና 11 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ የሚገመት የዝሆን ጥርስ በመዲናዋ አቡጃ እንዲሰባበር አድርገዋል።
የናይጄሪያ ባለሥልጣናት 2.5 ሜትሪክ ቶን የሚመዝን እና 11 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ የሚገመት የዝሆን ጥርስ በመዲናዋ አቡጃ እንዲሰባበር አድርገዋል።

የናይጄሪያ ባለሥልጣናት 2.5 ሜትሪክ ቶን የሚመዝን እና 11 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ የሚገመት የዝሆን ጥርስ በመዲናዋ አቡጃ እንዲሰባበር አድርገዋል። ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት አደንን ለመከላከል ያለመ ርምጃ ነው ተብሏል።

ከሕገ ወጥ አዳኞች ላይ የተሰበሰበው እና ለዓመታት የተከማቸው የዝሆን ጥርስ ከተፈጨ በኋላ አስተማሪ የሚሆን ሃውልት እንደሚሰራ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ባለፈው ጥቅምት 4 ሜትሪክ ቶን የሚመዝን እና 1.4 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የዝሆን ጥርስ በተመሳሳይ መንገድ እንዲፈጭ ተደርጓል።

በሕገ ወጥ አደን ምክንያት በናይጄሪያ የሚገኙ ዝሆኖች ብዛት ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ከ1ሺሕ 500 ወደ 400 ዝቅ ማለቱ ታውቋል።

ሕግ አስከባሪዎች እንደሚሉት፣ በሕገ ወጥ መንገድ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ወደ እስያ የሚልኩ ወሮበሎች ናይጄሪያን እንደ ዋና ምንጭ ይጠቀማሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG