በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በውጭ ሀገር የሚኖሩ ናይጄሪያውን ድምጽ ለመስጠት ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ናይጄሪያ ውስጥ የፊታችን ቅዳሜ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ናይጄሪያውያን ድምጽ እንዲሰጡ እንዲፈቀድ እንግሊዝ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት ናይጄሪያውያን ያቀረቡትን ጥያቄ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገው፡፡

“በህገ መንግሥቱ መሠረት የመምረጥ መብት ያላቸው ናይጄሪያ ውስጥ የሚኖሩ የተመዘገቡ ናይጄሪያውያን ብቻ ናቸው” በማለት ፍርድ ቤቱ የሁለቱን ናይጄሪያውያን አቤቱታ ውድቅ አድርጎባቸዋል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ናይጄሪያውያን በየዓመቱ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ወደሀገራቸው በመላክ ለኢኮኖሚው አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ሲሆን የሁለቱ ናይጄሪያውያን አቤቱታ ደጋፊዎች በውጭ ባሉ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች ድምጻቸውን መስጠት እንዲችሉ ህገ መንግሥቱ መሻሻል እንዳለበት ይስማማሉ፡፡

የናይጄሪያው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ በውጭ ሀገሮች የሚኖሩ ናይጄሪያውያን ድምጽ መስጠት መቻል እንዳለባቸው የሚስማማበት መሆኑን ገልጾ ሆኖም የሚፈቅዱት ፍርድ ቤቶች ሳይሆኑ የፓርላማ አባላቱ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG