በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ውስጥ 85 ሰዎች በተገደሉበት የድሮን ጥቃት ምርመራ እንዲከፈት ፕሬዚደንቱ አሳሰቡ


ፕሬዚደንት ቦላ ቲኑቡ
ፕሬዚደንት ቦላ ቲኑቡ

የናይጄሪያ የጦር ሠራዊት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአንድ የሀገሪቱ መንደር ስላደረሰው የድሮን ጥቃት ምርመራ እንዲከፈት የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ቦላ ቲኑቡ ማሳሰባቸው ተገልጧል፡፡

የድሮን ጥቃቱ የደረሰው በሰሜናዊዋ ካዱና ክፍለ ግዛት ቱዱን ቢሪ የተባለች መንደር ነዋሪዎች ከትናንት በስተያ ዕሁድ በአንድ የእስልምና ዕምነት በዐል በማክበር ላይ ሳሉ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በርካታ ነዋሪዎች ቆስለዋል፡፡

ፕሬዚደንት ቲኑቡ ጥቃቱን “እጅግ የሚያሳዝን” ብለው ምርመራ እንዲከፈት ማሳሰባቸውን ከጽሕፈት ቤታቸው የወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

የናይጄሪያ የአየር ኃይል በጥቃቱ እጄ የለበትም ብሏል፡፡

የናይጄሪያ የጦር ኃይል በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቃዊ እና ሰሜን ምዕራባዊ ክፍለ ግዛቶች ለበርካታ አሰርት ሽምቅ ውጊያ ላይ ከሚገኙት ጽንፈኛ እስላማዊ ታጣቂዎች ጋር በሚያካሂደው ውጊያ በተደጋጋሚ አብራሪ አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች ሲጠቀም መቆየቱ ይታወቃል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG