ናይጄሪያ የቦኮ ሃራሞችን ጭካኔ የተመላበት ዓመፅ እየተዋጋች ባለችበት በአሁኑ ወቅት የጦር ኃይሏ የዚያኑ ያህል አደገኛ የሆነ ጠላት ሙስና እያሰነካከለው ነው።
ፅህፈት ቤቱ ጀርመን የሆነው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሠረት የናይጄሪያ ወታደራዊ መኮንኖች ፖለቲከኞች እና ሌሎችም ከፍተኛ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የታለመ ገንዘብ እየወሰዱ ወደኪሳቸው ከትተው ከብረውበታል ብሏል።
ገንዘቡ በጉቦ በሌሉ ወታደሮች ስም በሚከፈል ደመወዝ መልክ እንደሚባክን ሪፖርቱ አውስቷል።
ከመንግሥት ጋር ትሥሥር ላላቸው የሥራ ተቆራጮች ኮንትራት ያለጨረታ እየተሰጠ፣ መጠነ ሰፊ ገንዘብ በሙስና ይወድማል ሲልም አስረድቷል።
በተጭበረበረ የጦር መሣሪያ ግዢ ውል የጠፋው ገንዘብ አሥራ አምስት ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ብለው እንደሚያምኑ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ገልፀዋል።
የናይጄሪያ የመከላከያ መረጃ ኃላፊ ሜጀር ጄነኢራል ጆን ኤንንች በበኩላቸው ሪፖርቱ አሳዛኝና ከዕውነት የራቀ ነው ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ