ዋሺንግተን ዲሲ —
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ዛሬ በተናገሩት ቃል፣ ምንም እንኳ ተቀናቃኛቸው ቅሬታ ቢኖራቸውም፣ ለሌላ አራት ዓመት ለሥልጣን ያበቃቸው የአሁኑ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ግን ምንም ውዝግብ እንደሌለበት አስታወቁ።
ቡሃሪ ይህን ያስታወቁት፣ አቡጃ ውስጥ በሚገኘው በብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት መሆኑም ታውቋል።
ነፃው የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ረቡዕ ይፋ እንዳደረገው፣ የ76 ዓመቱ ቡሃሪ፣ በቅዳሜው ምርጫ አሸናፊ ናቸው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ