በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሙሃማዱ ቡሃሪ የቦኮ ሃራም አማፅያን የሚደቅኑት አደጋ ቀንሷል አሉ


የናይጀርያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ
የናይጀርያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ

የናይጀርያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የቦኮ ሃራም አማፅያን የሚደቅኑት አደጋ እየቀነሰ ሄዶ ሰዎች ወደ ቀያቸውና ወደ እርሸቸው እየተመለሱ በመሆናቸው በሀገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ ኑሮ እየተሻሻለ ሄዷል ብለዋል።

የናይጀርያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የቦኮ ሃራም አማፅያን የሚደቅኑት አደጋ እየቀነሰ ሄዶ ሰዎች ወደ ቀያቸውና ወደ እርሸቸው እየተመለሱ በመሆናቸው በሀገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ ኑሮ እየተሻሻለ ሄዷል ብለዋል።

ቡሃሪ ትላንት በአሜሪካ ድምፅ በተደረገላቸው ቃለመጠይቅ ሲናገሩ ቦኮ ሃራም በሚያደርሰው ጥቃት ምክንያት ከሰሜን ምሥራቁ ክፍል ሸሽተው የነበሩት በርካታ ናይጀርያውን ወደ መኖርያቸው መመለሳቸውን ጠቁመዋል። መንግሥት በዝቅተኛ ወለድ በሚሰጠው ብድር እርሻቸው ላይ እየዘሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ከሦስት ዓመታት በፊት ቡሃሪ ሥልጣን ላይ በወጡበት ወቅት ቦኮ ሃራም በቦርኖ ክፍለ-ሀገር ያሉትን አብዛኛቹን የመንግሥት አከባቢዎችን ይቆጣጠር እንደነበር ገልፀዋል። አሁን ግን የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል በነገረኝ መሰረት ቦኮ ሃራም የሚቆጣጠረው የመንግሥት ቦት የለም። ወታደራዊው ኃይል ያለውን አምናለሁ ሲሉ ቡሃሪ ተናግረዋል።

ቦኮ ሃራም አሁንም በሰሜን ምሥራቅ ናይጀርያና በጎረቤት ሀገር ካሜሩን ይንቀሳቀሳል። ነገር ግን ናይጀርያንና አራት ጎረቤቶች ሀገሮችን ባካተተው የኅብረ ብሄራት ግብረ ኃይል በሚወስድበት እርምጃ ምክንያት ክፉኛ ተዳክሟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG