በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"አልሞትኩም" - ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ


ሙሐማዱ ቡሃሪ /የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት - ፎቶ ፋይል/
ሙሐማዱ ቡሃሪ /የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት - ፎቶ ፋይል/

"'ሞተ' ያሉት ማይሞችና አረማዊያን ናቸው" ብለዋል የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ በማኅበራዊ ሚድያ ሲናፈስባቸው የቆየውን ሃሜት ሲያስተባብሉ።

"'ሞተ' ያሉት ማይሞችና አረማዊያን ናቸው" ብለዋል የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ በማኅበራዊ ሚድያ ሲናፈስባቸው የቆየውን ሃሜት ሲያስተባብሉ።

እንግሊዝ ውስጥ ለአምስት ወራት ለሕክምና የቆዩት ፕሬዚዳንት ቡሃሪ ‘ሞተዋል፤ በቦታቸውም ፍፁም እርሣቸውን የሚመስል ሱዳናዊ ተተክቷል’ እየተባለ ‘የተነዛው አሉባልታ ጨርሶ ሃሰተኛ’ መሆኑን ትናንት ዕሁድ ፖላንድ ውስጥ በዳያስፖራ ለሚገኙ የሃገራቸው ተወላጆች ተናግረዋል።

ሙሃማዱ ቡሃሪ ፖላንድ የገቡት ካቶቪፀ በምትባለው የፖላንድ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ለመጭዎቹ ሁለት ሣምንታት በሚካሄደው 24ኛው የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ ለመሣተፍ ነው።

«እኔ - የእውነቱ እራሴ ነኝ፣ ይሄንን አረጋግጥላችኋለሁ» ሲሉ የመሃላ ያህል ‘በእኔ ይሁንባችሁ’ ያሉት ቡሃሪ «በቅርቡም 76ኛውን የልደቴን ቀን አከብራለሁ፤ እንዲሁ ጠንካራ ሆኜም እቀጥላለሁ» ብለዋል።

“ብዙ ሰዎች’ኮ ታምሜ ሳለሁ ሞቴን ተመኝተው ነበር፤ አንዳንዶች እንዲያውም ‘ሞቷል’ ብለው በማመናቸው ወደ ምክትሌ እየሄዱ ለምክትልነት እንዲያጫቸው አመልክተዋል” ማለታቸውን ቃል አቀባያቸው ባወጡት መግለጫ ጠቁመዋል።

የፈጠራ ወሬው የተናፈሰው ቡሃሪ በህመም ምክንያት በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር 2017 ዓ.ም አብዛኛውን ጊዜ ሎንዶን በህክምና በማሳለፋቸው እንደሆነም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG