ባለፈው ቅዳሜ በናይጄሪያ የተደረገው ምርጫ በመቆጠር ላይ ሲሆን፣ ፒተር ኦቢ የተባሉ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪ የሌጎስን ግዛት እንዳሸነፉ ዛሬ ሰኞ ቀድመው የወጡ ውጤቶች አሳይተዋል፡፡
የሠራተኛ ፓርቲው ወኪልና ለፖለቲካው መድረክ አዲስ የሆኑት ፒተር ኦቢ ሌጎስን ማሸነፍ ላለፉት 20 ዓመታት ፖለቲካውን ተቆጣጥረዋት የነበሩትን ሁለት ፓርቲዎች የተገዳደረ ነው ተብሏል፡፡
የተሰናባሽቹ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የሆነው ገዢው ‘ኦል ፕሮግረሲቭ ኮንግረስ’ እና ዋናው ተቃዋሚ ‘ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ ናይጄሪያ ከወታደራዊ አገዛዝ ከተላቀቀችበ እ.አ.አ 1999 ጀምሮ አገሪቱን ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል፡፡
በሰሜን በምትገኘውና ፖርት ሃርኮርት በተሰኘችው ከተማ በደርዘን የሚቆጠሩ ድምጽ ሰጪዎች የምርጫ አስፈጻሚዎች ጥቅም ላይ ያልዋሉትን ድምጽ መስጫ ወረቀጦች እንዲያቃጥሉ ሲወተውቱ ተስተውለዋል፡፡ ወረቀቱ ደግሞ እንዳይቆጠር እየተከላልን ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፤
ድምጽ አሰጣጡ በአብዛኛው ሰላማዊ እንደነበር ሲነገር፣ ውጤቶችን ወደ ማዕከላዊ ቢሮው አውታር የመጫኑ ሂደት ግን መዘግየት ታይቶበታል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ናይጄሪያውያን በተጨማሪም በቅዳሜው ምርጫ የተወካዮች ም/ቤትንና የህግ መወሰኛ ም/ቤት ለመምረጥ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
90 ሚሊዮን የሚሆኑ ድምጽ ሰጪዎች ባሏት ናይጄሪያ፣ አዲሱ ፕሬዚዳንት አገሪቱን ከተባባሰው የጸጥታ ችግር፣ የኢኮኖሚ ቀውስና ድህነት እንዲታደጋቸው ዜጎቿ ይሻሉ።
ናይጄሪያውያን የሚመርጡት አገሪቱ በአክራሪዎችና ተገንጣዮች ጥቃት እየደረሰባት፣ የተዳከመ ኢክኖሚ ባለበትና ድህነት በተንሰራፋበት ወቅት በመሆኑ ለለውጥ ያለው ጉጉት ከፍተኛ ነው።