በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የፋሽን ትርዒት” በአፍሪካ አረጋውያን

አንድ ናይጄሪያዊ የጥበብ ሰው፣ ሰው ሰራሽ ልዕቀትን በመጠቀም አፍሪካዊ አረጋውያንን የፋሽን ሞዴል አድርጎ በማቅረቡ በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።
አንድ ናይጄሪያዊ የጥበብ ሰው፣ ሰው ሰራሽ ልዕቀትን በመጠቀም አፍሪካዊ አረጋውያንን የፋሽን ሞዴል አድርጎ በማቅረቡ በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።

አንድ ናይጄሪያዊ የጥበብ ሰው፣ ሰው ሰራሽ ልዕቀትን በመጠቀም አፍሪካዊ አረጋውያንን የፋሽን ሞዴል አድርጎ በማቅረቡ በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።

የናይጄሪያዊው ማሊክ አፌግቧ የፈጠራ ሥራዎች፣ አፍሪካዊ አረጋውያን ዘወትር የሚታዩበትን ሁኔታ የቀየረ እና ፀጋ እና ውበታቸውን ያሳየ ነው ተብሏል።

በሰው ሰራሽ ልዕቀት የተፈጠሩትና በዘመናዊ አልባሳት የተዋቡት አረጋውያን ፎቶዎችን “የአረጋውያን ፋሽን ትርዒት” ሲል ገልጿቸዋል ፈጣሪው።

የፊልም ባለሙያው ማሊክ ሥራዎቹ አፍሪካዊ አረጋውያን በአብዛኛው በማይታዩበት መንገድ እንዳቀረባቸው ተናግሯል። ሃሳቡን ያገኘውም በሕመም በመሰቃየት ላይ ካለች እናቱ እንደሆነ ማሊክ ተናግሯል።

የ’ብላክ ፓንተር’ ፊልም የልብስ ንድፍ ኦስካር ሽልማት አሸናፊን ጨምሮ ሌሎችንም ታዋቂ የልብስ ነዳፊዎችን ትኩረት ማግኘቱን እና በትብብር መሥራት መጀመሩም ታውቋል።

በአምስተርዳም በተደረግው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት፣ የሰው ሰራሽ ልዕቀትን ሳይሆን፣ እውነተኛ አረጋውያንን በመጠቀም ትዕይንቱን አቅርቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG