በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒዤር ሁንታው የአገሪቱን የአየር ክልል ዘጋ


ኒያሚ፣ ኒዤር
ኒያሚ፣ ኒዤር

በኒዤር፣ ከሳምንት በፊት፣ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ከሥልጣን ያስወገደው ሁንታ፣ የአገሪቱን የአየር ክልል ዘግቷል።

የሁንታው ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሜጄር አማዱ አብድራሜ፣ “በጎረቤት ሀገራት ጣልቃ የመግባት ዝግጅት እየተካሔደ በመኾኑ፣ ሌላ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ፣ የአየር ክልሉ ተዘግቷል፤” ሲሉ አስታውቀዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም፣ “በአገሪቱ ሰማይ ላይ የሚደረግ ማንኛውም የበረራ ሙከራ፣ የወዲያው ምላሽ ይሰጠዋል፤” ሲሉ ዝተዋል።

“ሁለት የማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት፣ ወረራ ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ ናቸው፤” ሲል፣ ሁንታው ክሥ አሰምቷል። አገራቱን ግን በስም ከመግለጽ ተቆጥቧል።

የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ(ኤኮዋስ) በበኩሉ፣ እስከ ትላንት እሑድ ድረስ፣ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ባዙም ወደ ሥልጣን እንዲመለሱ ቀነ ገደብ አስቀምጦ የነበረ ሲኾን፣ ወታደራዊ ኃይል በመጠቀም ጣልቃ እንደሚገባ ዝቷል።

ኤኮዋስ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ማለፉን ተከትሎ፣ አባል ሀገራቱ፣ በመጪው ኀሙስ፣ የመሪዎች ስብሰባ በማድረግ በቀጣይ ርምጃዎች ላይ እንደሚወያይ አስታውቋል።

የሁንታውን የአየር ክልል እገዳ ተከትሎ፣ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች፣ የኒዤር ሰማይን ሳይነኩ ማለፍ እንደጀመሩ፣ የአሶሺዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG