በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዛሬው የኒጀር ሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመጀመሪያው ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ተስፋ አሳድሯል


NIGER-POLITICS-VOTE supporters of Mohamed Bazoum ahead of the presidential runoff
NIGER-POLITICS-VOTE supporters of Mohamed Bazoum ahead of the presidential runoff

በኒጀር የሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች በዛሬው ዕለት ድምጻቸውን ሲሰጡ ውለዋል። በመዲናይቱ ኒያሚ የኮቪድ መከላከያ የፊት መሸፈኛ ጭምብል ያደርጉትን ጨምሮ መራጮች በአቧራማ የትምህርት ቤቶች ሜዳዎች ተሰልፈው ድምጻቸውን ለመስጠት ሲጠባበቁ ተስተውለዋል።

የዘንድሮው ምርጫ ምዕራብ አፍሪቃዊቱን አገር ነጻ ከወጣችበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1960 ዓም ወዲህ የመጀመሪያዋ ለሆነው ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር የሚያበቃ ይሆናል ተብሎ ተጠብቋል። ባለፈው ታህሳስ መገባደጂያ በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ 39.3 በመቶውን የመራጭ ድምጽ በማግኘት ብልጫ ያስመዘገቡት የገዢው ፓርቲ ዕጩ ሞሃመድ ባዙም የብዙዎችን ይሁንታ አግኝተዋል።

በተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ማሃማዱ ኢሱፍ አስተዳደር የውጭ እና የአገር ውስጥ ሚንስትርነትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነት የሰሩትን ባዙም በቀደመው ዙር የ17 በመቶውን የመራጭ ድምጽ ብቻ ያገኙትን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሞሃመኔ ኦስማኔን ነው በዳግም ምርጫ ፉክክር የሚገጥሙት።

ባዙም በመጀመሪያ ዙር ፍክክር የ3ተኛ እና የአራተኛውን ደረጃ ይዘው የነበሩትን ዕጩዎችንም ድጋፍ አግኝተዋል።

ተቀናቃኛቸው የ71 ዓመቱ ኦስማኔ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለስልጣን ሲበቁ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሲሆኑ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጣር በ1996 በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ነበር ከስልጣን የተወገዱት።

XS
SM
MD
LG