በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒዤር ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ፥ መሃመዱ ኢሱፉ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በከፊል የወጡ ውጤቶች አመለከቱ 


የኒዤር ፕሬዝዳንት መሃመዱ ኢሱፉ ( Mahamadou Issoufou)
የኒዤር ፕሬዝዳንት መሃመዱ ኢሱፉ ( Mahamadou Issoufou)

በሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገባ መሠረት፥ የኒዤር ምርጫ ኮሚሽን እስካሁን በተካሄዱ ቆጠራዎች፥ ኢሶፉ ከመቶ 93 ድምፅ አግኝተዋል ብሏል።

በኒዤር ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ፥ የወቅቱ መሪ መሃመዱ ኢሱፉ (Mahamadou Issoufou) በከፍተኛ የድምፅ ብልጫ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ፥ በከፊል የወጡ ውጤቶች አመለከቱ።

በሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገባ መሠረት፥ የኒዤር ምርጫ ኮሚሽን እስካሁን በተካሄዱ ቆጠራዎች፥ ኢሶፉ ከመቶ 93 ድምፅ አግኝተዋል ብሏል። በኒዤሩ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ዘንድሮ ድምፅ ለመስጠት የወጣው ብቁ መራጭ 61 ከመቶ እንደሚደርስም ኮሚሽኑ አብራርቷል።

ሕዝቡ በእሁዱ ምርጫ እንዳይሳተፍ ጥሪ ያቀረበው የተቃዋሚ ፓርቲ፥ ውጤቶቹ ተዓማኒ አይደሉም ብሏል። በኒዤር ያሜሪካ ድምፁ ዘጋቢም በመላ ሃገሪቱ ዙሪያ የታየው የመራጭ ሕዝብ ብዛት በጣም አነስተኛ እንደነበር በእሁድ ሪፖርቱ ገልጿል።

COPA 2016 የተሰኘው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ቃል አቀባይ ኦሴኒ ሳላቱ (Ousseini Salatou) ሲናገሩ ደግሞ፥ ደጋፊዎቻችን ድምፅ ለመስጠት ባልወጡበት ምርጫ፥ ውጤቶች አስመልክቶ የተሰጡ አሃዞች ”አሳፋሪ” ናቸው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG