በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ፈረንሣይ ጣልቃ ልትገባ እያሴረች ነው” - የኒዤር ጁንታ

በኒዤር ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንቱን አስወግዶ ሥልጣን የተቆጣጠረው ጁንታ፣ “ፈረንሣይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በመፈጸም ፕሬዝደንት ሞሃመድ ባዙምን ወደ ሥልጣን መመለስ ትሻለች” ሲል ከሰሰ።

የምዕራቡ ዓለም ሸሪክ የሆኑትና ከሁለት ዓመታት በፊት በምርጫ ሥልጣን የጨበጡት ባዙም፣ በፕሬዝደንታዊ የጥበቃ ኃይሉ ከሥልጣናቸው የተወገዱት ባለፈው ረቡዕ ነበር።

የፕሬዝደንታዊ ጥበቃ ኃላፊው ጄኔራል አብዱራሃማኔ ቲያኒ፣ ሃገሪቱን የሚመሩት እርሳቸው እንደሆኑ በሳምንቱ መጨረሻ አስታውቀዋል። ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ድርጊቱን ሲያወግዝ፣ የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ፣ በምሕጻሩ ECOWAS ወታደራዊ ቡድኑ ስልጣኑን በአንድ ሣምንት ውስጥ ለፕሬዝደንት ባዙም መልሶ እንዲያስረክብ የግዜ ገደብ አስቀምጧል።

ትናንት ዕሁድ በፈረንሣይ ኤምባሲ የተሰባሰቡ ተቃዋሚዎች ወደ ግቢው ዘልቀው ለመግባት ሲሞክሩ በአስለቃሽ ጭስ ተበትነዋል። በፈረንሣይ ዜጎች እና ንብረት ላይ ጥቃት ቢደርስ “አስቸኳይ እና የማያወላውል” ርምጃ እንደሚወሥዱ የፈረንሣዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን አስጠንቅቀዋል።

ጁንታው ዛሬ ሰኞ “ፈረንሣይ ጣልቃ ለመግባት እያሴረች ነው” ሲል ከሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG