በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜዲትራኒያን ባህር ላይ በትናንሽ ጀልባዎች ላይ የሚጓዙ ፍልሰተኞች ቁጥር እየጨመረ ነው


 የአፍሪካ ፍልሰተኞች በሊቢያ እና ቱኒዚያ ድንበር በባህር ዳርቻ በራስ ጄድር እአአ መስከረም 26/2023
የአፍሪካ ፍልሰተኞች በሊቢያ እና ቱኒዚያ ድንበር በባህር ዳርቻ በራስ ጄድር እአአ መስከረም 26/2023

ከፈንጆቹ ገና በኃላ የአየሩ ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን ተከትሎ፣ ወደ ጣሊያን ባህር ዳርቻ የሚደርሱ ፍልሰተኞች ቁጥር እየጨምረ መምጣቱን የጣሊያን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ትላንት ያወጣው መረጃ አመልክቷል።

ከጣልያን የባህር ዳርቻዎች የሚደርሱ ፍልስተኞች ቁጥር የአየሩ ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ ከገና በዓል ወዲህ በድንገት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ መታየቱን ከጣልያን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ትናንት ሐሙስ የወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

ባለፉት አራት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ1 ሺህ 500 በላይ ስደተኞች መመዝገባቸውንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፍልሰተኞች የተመዘገቡት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ሲሆን፣ በእለቱ ጣሊያን ባህር ዳርቻ ላይ የደረሰኡት ሰዎች ቁጥር 723 መሆኑ ተገልጿል። አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ከቱኒይዚያ በ130 ኪሊሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ላምፔዱሳ ደሴት ማረፋቸውም ተመልክቷል።

የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚያንቀሳቅሷቸው በርካታ የነፍስ አድን መርከቦችም ከገና በዓል ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በማዕከላዊ ሜዲትራኒያን ባህር ታድገዋል። በገና ምሽት በተካሄደው የመጀመሪያው የነፍስ አድን ስራ፣ የባህር ጠባቂዎች በማዕከላዊ ሜዲትራኒያን ባህር ላይ የሦስት ዓመት ህፃንን ጨምሮ 118 ታዳጊዎችን ማዳን ችለዋል። የኤስኦ ኤስ ሜዲቴራኒያን ቡድን በበኩሉ ከትናንት በስትያ 244 ሰዎችን ማዳኑን ገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ኤጀንሲ (UNHCR) እንደገለጸው ከ2023 መጀመሪያ ጀምሮ 260,662 ሰዎች የሜዲትራኒያን ባህር አቋርጠው ከሰሜን አፍሪካ አውሮፓ ደርሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG