በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ሰሜን ወሎ 19 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሞቱ 24 ቆሰሉ


በሰሜን ወሎ ባለፈዉ ሳምንት የጣለዉ ዝናብ ያስከተለዉ ጎርፍ 19 ሰዎች ገድሎ በ24 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ማድረሱን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ

የአፋርንና የሰሜን ሱማሌን ክልልች የሚያዋስኑትን የአማራ ቆላማ ስፍራዎችን ጨምሮ፣ በአገሪቱ ዉስጥ ባለፉት ጥቂት ቀናት አዳዲስ የጎርፍ ማጥለቅለቅ መድረሱን በተባበሩት መንግስታት ድር፡ጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታዉቋል። በሰሜን ወሎ ዞን ባለፈዉ ነሃሴ 16 የጣለዉ ዝናብ ያስከተለዉ መሬት መንሸራተት የ19 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉንና 24ቱን ማቁሰሉን የአካባቢዉን የዞኑን የመንግስት ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቦአል። በአካባቢዉ በሽህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአካባቢአቸዉ እንደተፈናቀሉና አንዳንዶችም በጎርፉ የተከበቡ በመሆኖቸዉ ሁኔታዉን ለመገምገምና እርዳታም ለማቅረብ እንዳለተቻለ የስብአዊ ጉዳዮች ጽህፈት ቤቱ አስግንዝቦአል። በዚህ ክልል ብቻ የተጎጂዉ ህዝብ ቁጥር እስከ 270 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል የተጠቀሰ ሲሆን በሚቀጥሉት የክረምቱ ሳምንታት የጎርፍ አደጋዉ በአብዛኛዉ የአገሪቱ ክፍሎች ሊስፋፋ እንደሚችል የስብአዊ እርዳታ ጽህፈት ቤቱ መግለጫ ጠቁሞአል።

XS
SM
MD
LG