በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒውዚላንድ የተገደሉ ሰዎች አስከሬኖች ለቤተሰብ ማስረከብ ተጀመረ


የኒውዚላንድዋ ክራይስትቸርች ከተማ ባለሥልጣናት ባለፈው ዓርብ በሁለቱ መስጊዶች በነጭ ብሄርተኛ እጅ የተገደሉትን ሃምሳ ሰዎች አስከሬኖች ለቤተሰብ ማስረከብ ጀምረዋል።

ፖሊሶች እንዳስታወቁት የሁሉም ሰለባዎች አስከሬኖች ምርመራ ተጠናቋል። ማንነታቸው ተለይቶ የታወቀው ግን አስራ ሁለቱ ብቻ ናቸው። ከአስራ ሁለቱ መካከል የስድስቱን ቤተሰብ ተረክቧል።

የክራይስትቸርች ፖሊሶች ሲያስረዱ የአስከሬን መለየቱ ሥራ ቀጥተኛ ቢመስልም በተለይ እንደዚያ ባለ ሁኔታ ውስብስብ እንደሆነ ገልጸዋል። እስካሁን የጥቃቱ ሰለባዎች ስም ለቤተሰብ የተሰጠ ቢሆንም ስም ዝርዝራቸው ይፋ አልተደረገም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG